Skip to main content

የመርዛማ ውጋጅ መረጃ እና አገልግሎቶች

የሚኖሩት ወይም የሚሰሩት ኪንግ ካውንቲ ውስጥ ከሆነ፣ ራስዎን እና አካባቢዎን ከመርዛማ ውጋጅ እንዲከላከሉ ለመርዳት ምቹ የሆኑ አደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ ዘዴዎችን እና መረጃዎችን እናቀርብልዎታለን።

a mother and son in a grocery store aisle

የተለመዱ መርዛማ ምርቶች

ያልተጠቀምንባቸው፣ ያረጁ ወይም አስፈላጊ ያልሆኑ መርዛማ ምርቶችን ማስቀመጥ አደገኛ ሊሆን ይችላል። እነዚህ ምርቶች ከቆሻሻ ጋር ከተጣሉ ወይም ከፍሳሽ ማስተላለፊያ ጋር ከተቀላቀሉ በሰዎችም ሆነ አካባቢ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ። መርዛማ ምርቶች መሆን አለመሆናቸውን የምርቶቹ ተለጣፊ ምልክት ላይ ማንበብ ይችላሉ። እነዚህ መርዛማ ምርቶች ተለጣፊ ምልክት አላቸው ይህም danger (አደገኛ) poison (መርዝ) warning (ማስጠንቀቂያ) ፣ ወይም caution (ጥንቃቄ) የሚሉ ቃላቶችን ይይዛል።

 

Icon of bottles with the EPA Safer Choice logo and Cradle to Cradle logo

ደህንነቱ የተረጋገጠ

እነዚህ ዓርማዎች በፊት ለፊት ወይም በጀርባ በኩል ያሉበትን ምርት ያግኙ።

እባክዎ ያስታውሱ፡- የEPA Safer Choice ምርቶች፣ CAUTION (ጥንቃቄ) የሚል ቃል ቢጻፍባቸውም ለደህንነት አስተማማኝ ናቸው።

Icon of a bottle that does not have the words caution, warning, danger, or poison on the label

ጎጂ ያልሆነ

CAUTION (ጥንቃቄ)፣WARNING (ማስጠንቀቂያ)፣DANGER (አደገኛ) ወይም POISON (መርዝ) የሚሉት ቃላት ያልተጻፉበት ምርት ይምረጡ።

Icon of a bottle with the words Caution and Warning

በተወሰነ ደረጃ ጎጂ

CAUTION (ጥንቃቄ) ወይም WARNING (ማስጠንቀቂያ) የሚሉት ቃላት የተጻፈበት ምርት ይምረጡ።

Icon of a bottle with the words Danger and Poison

በጣም ጎጂ - ይቆጠቡ

DANGER (አደገኛ) ወይም POISON (መርዝ) የሚሉት ቃላት የተጻፈበት ምርት ከመጠቀም ይቆጠቡ። ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ ከምንም በላይ ጎጂ ናቸው።

ደህንነቱ የተጠበቀ አወጋገድ 3 ደረጃዎች

Staff person wearing protective gear unloads hazardous wastes from the trunk of a car
step 1

እቃዎቹን ይሰብስቡ፡

ልጥፉ የሚከተሉት ቃላት ካሉት DANGER (አደገኛ)POISON (መርዝ) WARNING (ማስጠንቀቂያ) ፣ ወይም CAUTION (ጥንቃቄ) ፣ ይህ መርዛማ ውጋጅ ነው።

የምንቀበላቸውን የእቃዎች ዝርዝር ይመልከቱ።

step 2

ለማስወገድ የሚደረጉ ዝግጅቶች፡፡

የሚወገዱትን እቃዎች በራሳቸው መያዣ ውስጥ ያስቀምጡ፣ ምርቶቹ ምልክት ካልተደረገባቸው ምልክት ያድርጉባቸው እንዲሁም ምርቶቹ እንዳይንጠባጠቡ ወይም እንዳይፈሱ በጥንቃቄ ይዝጉ። ምርቶቹን ከተሸከርካሪዎ የተሳፋሪዎች መቀመጫ አርቀው ያስቀምጡ።

step 3

ማስወገጃ ቦታ፡-

የሚወገዱትን እቃዎች ወደ ማስወገጃ ቦታ ያምጡ። አገልግሎቱ በእርስዎ የአገልግሎት ክፍያ አማካኝነት የሚሸፈን በመሆኑ ምንም ክፍያ አይከፍሉም።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የማስወገጃ ቦታ ይፈልጉ።

 • North Seattle
  እሁድ – ማክሰኞ

  12550 Stone Ave N Seattle, WA 98133
  9:00 a.m. – 5:00 p.m.

  ጁላይ 4፣ ታንክስጊቪንግ ቀን (Thanksgiving Day)፣ በገና በአል እና በአዲስ አመት ቀን ዝግ ይሆናል።

 • South Seattle
  ሐሙስ – ቅዳሜ

  8100 2nd Ave S Seattle, WA 98108
  9:00 a.m. - 5:00 p.m.

  ከቆሻሻ ማስወገጃ ጣቢያ አጠገብ ይገኛል
  ጁላይ 4፣ ምስጋና በምናቀርብበት ቀን፣ በገና በአል እና በአዲስ አመት ቀን ዝግ ይሆናል።

 • Factoria
  ማክሰኞ – ዓርብ፥ ቅዳሜ እና እሁድ

  13800 SE 32nd St. Bellevue, WA 98005
  8 a.m. – 4 p.m. (ማክሰኞ-ዓርብ)፥ 9 a.m. – 5 p.m. (ቅዳሜ-እሁድ)

  የፋክቶርያ ተቋም በቆሻሻ ማስወገጃ ጣቢያ አጠገብ ይገኛል። ምስጋና የምናቀርብበት ቀን ፣ በገና በአልና በአዲስ አመት ዝግ ይሆናል።

 • Auburn
  ቅዳሜ - እሁድ

  1101 Outlet Collection Way, Auburn, WA 98001
  10 a.m.–5 p.m.

  የኦበርን Wastemobile ዓመቱን ሙሉ ቅዳሜና እሁድ ክፍት ነው። የመርከበኛ የአደጋ ጊዜ አብረቅራቂዎች በዚህ ቦታ ተቀባይነት የላቸውም።
  ይህ አገልግሎት ከኖቬምበር 30፣ ዲሴምበር 1 እና ከዲሴምበር 28 - 29 አይገኝም።


Wastemobile - ተንቀሳቃሽ የመርዛማ ውጋጅ መሰብሰቢያ አገልግሎት


ይህ ነጻ የቆሻሻ መሰብሰብ አገልግሎት ለኪንግ ካውንቲ ነዋሪ ማህበረሰቦችን እና አነስተኛ የንግድ ስራዎችን የቤት ውስጥ መርዛማ ውጋጆቻቸውን የሚወስዱበት ምቹ ቦታ ለመምረጥ ጉብኝቶችን ያደርጋል።

 

የ ዌስትሞባይል ተዘዋዋሪ የቤተሰብ መርዛማ ውጋጅ ማንሻ አገልግሎት፣ ከእርስዎ አጠገብ የሚገኙ አካባቢዎችን የሚጎበኙበትን ጊዜ ይወቁ።

Graphic of a green car at a Wastemobile event

የቤት ለቤት መሰብሰብ ፕሮግራም

እድሜዎ ከ65 አመት በላይ ነው ወይም የአካል ጉዳተኛ ነዎት? ተሽከርካሪ ከሌለዎት እና ከዚህ ውጪ የመርዛማ ውጋጅ መሰብሰብያ ጣቢያ መሄድ የማይችሉ ከሆነ፣ ወደ እኛ በመደወል ከቤትዎ ቆሻሻ የማንሳት ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። የቤት ለቤት መሰብሰብ ፕሮግራም በእርስዎ የአገልግሎት ክፍያ አማካኝነት ይከፈላል፤ ስለሆነም ቆሻሻዎን ለማንሳት ክፍያ አይጠየቁም።የቆሻሻ ማንሻ ቀጠሮ ለማስያዝ፣ በሚከተለው ቁጥር ይደውሉ

206-296-4692

ሰኞ - ቅዳሜ፥ ከ 9 a.m. to 5 p.m. (ከበዓላት ውጪ) አስቀድሞ ከተጠየቀ የአስተርጓሚ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል

 

በኪንግ ካውንቲ ውስጥ የንግድ ድርጅት አለዎት?

የንግድ ባለቤት እንደመሆንዎ፣ አደጋን ሊያስከትል የሚችል ቆሻሻዎን በሰራተኞችዎ፣ ማህበረሰቡ ወይም አካባቢዎ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በአግባቡ ማስወገድ የእርስዎ ኃላፊነት ነው። ብቁ ለሆኑ የንግድ ስራዎች መርዛማ ውጋጃቸውን በነጻ እንዲያስወግዱ እገዛ ማድረግ እንችላለን። በተጨማሪም በቦታው በመገኘት የማማከር አገልግሎቶች፣ አካባቢን መሰረት ያደረጉ ምክሮች እና የማሻሻያ ተመላሽ ጥሬ ገንዘብ መስጠት እንችላለን። እነዚህ አገልግሎቶች በሙሉ ክፍያቸው በእርስዎ የአገልግሎት ክፍያ አማካኝነትስለሚሸፈን ለአገልግሎቶቹ ምንም ተጨማሪ ክፍያ አይጠየቁም።የበለጠ መረጃ ለማግኘት እና የንግድ ስራዎ ብቃቱን የሚያሟላ መሆኑን ለማወቅ እባክዎ በሚከተለው ይደውሉ

206-296-4692

ሰኞ - ቅዳሜ፥ ከ 9 a.m. to 5 p.m. (ከበዓላት ውጪ) አስቀድሞ ከተጠየቀ የአስተርጓሚ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል

የ ሃዝ ዌስት (Haz Waste) የእገዛ መስመር

ነዋሪዎችና የአነስተኛ የንግድ ስራ ባለቤቶች እንዴት መርዛማ ውጋጃቸውን በአግባቡ ማስወገድ እንዳለባቸው፣ መርዛማነታቸው አነስተኛ የሆኑ ምርቶችን መጠቀም እንዳለባቸውና ሌሎች ተያያዥ ርእሰ ጉዳዮችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት መደወል ይችላሉ።

ሰዓታት

ሰኞ - ቅዳሜ፥ ከ 9 a.m. to 5 p.m. (ከበዓላት ውጪ)

የ ሃዝ ዌስት (Haz Waste) የእገዛ መስመር
206-296-4692*

ኢሜል
haz.waste@kingcounty.gov

Garden Hotline

ነዋሪዎችና የቦታ ማስዋብ ሙያተኞች ስለ ቦታ ማስዋብ ጥያቄዎች ካሏችሁ ነጻ የሙያተኛ ምክር ለማግኘት ለGarden Hotline መደወል ይችላሉ።

ሰዓታት

ሰኞ - ቅዳሜ፥ ከ 9 a.m. to 5 p.m. (ከበዓላት ውጪ)

Garden Hotline
206-633-0224*

ድረ-ገጽ
gardenhotline.org

ስለ እኛ

ሃዛርደስ ዌስት ማኔጅመንት ፕሮግራም (Hazardous Waste Management Program) በአደገኛ ምርቶች አመራረት፣ አጠቃቀም፣ አቀማመጥ እና አወጋገድ የተነሳ የሚፈጠሩ ስጋቶችን በመቀነስ በኪንግ ካውንቲ ውስጥ የማህበረሰብ ጤናና የአካባቢ ንጽህናን ይጠብቃል እንዲሁም እንዲሻሻል ያደርጋል። የሲያትል ከተማን፣ 37 ሌሎች ከተሞችን፣ ሁለት ጎሳዎችን እና ያልተካተቱ ቦታዎችን ጨምሮ ለሁሉም የኪንግ ካውንቲ ነዋሪዎች አገልግሎት የምንሰጥ ክልላዊ ሸሪክ ነን።

 

በግንኙነት መስመር ላይ ይቆዩ

ዌስትሞባይል በአካባቢዎ የሚሆንበትን ጊዜ በተመለከተ አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎችን ለማግኘት ይመዝገቡ። እባክዎ፣ ጽሑፉ የሚዘጋጀው በእንግሊዝኛ እንደሆነ ይገንዘቡ።